Fana: At a Speed of Life!

ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ህዝቡ አንድነቱን አጠናከሮ ሊሰራ ይገባል – አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ዘላቂ ሠላምና ልማት መረጋገጥ ህዝቡ አንድነቱን አጠናከሮ ሊሰራ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አሳሰቡ።
ሀገር አቀፍ የማህበረሰብ ተኮር የውይይት መድረክ በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።
በውይይቱ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደተናገሩት የህወሓት ቡድን ባለፉት ዓመታት የተዛቡ ትርክቶችንና ከፋፋይ አስተሳሰቦችን በመስበክ የህዝቦችን የአንድነትና የአብሮነት እሴት ለመሸርሸር ሲሰራ ቆይቷል።
ቡድኑ በተለይም የሌለውን ታሪክ በመፃፍና የጥላቻ ሀውልት በመገንባት ህዝቦችን ለማለያየትና ሀገር ለማፍረስ በሰራቸው እኩይ ተግባራት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወትና ንብረት እንዲጠፋ ማድረጉን አውስተዋል።
ባለፉት ዓመታት የህዝቦችን አንድነትና አብሮነት ለመሸርሸር ሲሰበኩ የቆዩ ከፋፋይ አስተሳሰቦችን በማስወገድ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ ህዝቡ በአንድነት አጠናክሮ ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቶማስ ቱት በበኩላቸው ÷የክልሉ ህዝብ በተለይም የጁንታው ቡድን ባለፉት ሁለት ዓመታት ግጭት ለመፍጠር ሲያደርግ የቆየውን ሙከራ በማክሸፍ ረገድ ያሳየው ቁርጠኝነት የሰላም ወዳድነቱ ማሳያ ነው ብለዋል።
በቀጣይም ህዝቡ አንድነቱና አብሮነቱን በማጠናከር ለክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሰራ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.