Fana: At a Speed of Life!

በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ሙሉ ወጪ የተገነባው ደባርቅ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የግንባታ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቀጣይ ወር ተማሪዎችን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በ13 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት 18 መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍት፣ ቤተ ሙከራዎች፣ የአስተዳደር ህንፃ፣ መጸዳጃ ቤትና ክሊኒክ ያሟላ ነው፡፡
የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን ፈንታ እንዳሉት÷ በቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት በከተማው የሚታየውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ችግር የሚፈታ ነው ፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ዘመን ተሻጋሪ እና ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን ጥራት ያላቸውን የግንባታ ቁሳቁሶችን ከመጠቀም ጀምሮ ተገቢ የሆነ የባለሙያ ክትትል ተደርጎለታል ተብሏል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመረዳት እድሉን መስጠቱ በከተማ አስተዳደሩ ተማሪዎችና መምህራን ስም ምስጋና ያቀረቡት የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈትቤት ኃላፊ ትምህርት ቤቱ አዲስ በመሆኑ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበርና ሌሎች ግብአቶችን ለማሟላት ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ግብአት ለማሟላት በሚደረገው ጥረት የሚመለከተው የመንግስት ተቋም፣ የአካባቢው ማህበረሰብና በውጭ ሀገር የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ድጋፍ እንዲያደርጉም የትምህርት ጽህፈት ቤቱ ጥሪ ማቅረቡን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.