Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት መምራት የሚያስችል መሪ ዕቅድ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማትን በዘላቂነት መምራት የሚያስችል ስፓሻል መሪ ዕቅድ ይፋ ተደረገ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሸን የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ዕድገት ለማሳካትና ለመምራት የሚያስችል ሀገራዊ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ስፓሻል ጥናት ረቂቅ ሪፖርት ላይ የውይይት መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በዚህ ወቅት ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ዘለቄታዊ ልማት የሚመራ ስፓሻል ጥናት መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ጥናቱ እንደ ሃገር የመጀመሪያ መሆኑንና ኢትዮጵያ ያላትን ሀብት የመሬት ሁኔታ በማየት የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

አሁን ያሉትን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመምራት ባለፈ ወደ ፊት የሚመሰረቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ከምስረታቸው ጀምሮ በማገዝና በመምራት ትልቅ አቅም ይፈጥራልም ነው ያሉት።

የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስና በየትኛው አካባቢ ምን ዓይነት ኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት አለበት የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.