Fana: At a Speed of Life!

በመተከል ዞን ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሰባት ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ሰባት የሚደርሱ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።
በዞኑ ከተፈጠረው ችግር ጋር ተያይዞ ኮማንድ ፖስቱ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ የስራ ሃላፊዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
አሁን ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ ኮሎኔል አያሌው በየነ ተናግረዋል።
ዞኑ ወደነበረበት ሰላም ለመመለስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም ጥሪ ቀርቧል።
በተያያዘም ቀጠናውን በበላይነት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጥፊዎች ላይ በወሰደው እርምጃ 42 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮሎኔል አያሌው ገልጸዋል።
በዞኑ ቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በጸረ ሰላም ኃይሎች በተከፈተ ተኩስ 100 ንጹሃን ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውንም ኮማንድ ፖስቱ ገልጿል፡፡
በአካባቢው በደረሰው የሰዎች ሞት እና ንብረት መውደም እስካሁን ያለው መረጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ትክክለኛውን መረጃ የማጣራቱ ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
በደረሰው አደጋም ኮማንድ ፖስቱ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን መግለጹን ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በትናንትናው ዕለት ድርጊቱን የፈጸሙት ብሄረሰቡን የማይወክሉ እና ለውጡን የማይፈልጉ የጉሙዝ ሽፍታዎች እንደሆኑም ተገልጿል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.