Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በኢንቫይሮመንታል ሳይንስ እና ተያያዥ የትምህርት ዘርፍ ከ500 በላይ ወጣቶች ስልጠና እየተሰጣቸው ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ500 በላይ ወጣቶች ከ92 ሚሊየን ብር በላይ በጀት መድቦ በኢንቫይሮመንታል ሳይንስ እና ተያያዥ በሆነ የትምህርት ዘርፍ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ወጣቶቹ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ስራ የሌላቸው ሲሆኑ ከሁሉም ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ተውጣተው በማህበር የተደራጁ ናቸው።

ወጣቶቹ ወደ ስራ ሲገቡ በየክፍለ ከተማው እና በየወረዳው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎችን እና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚያደርሱትን የአካባቢ ብክለት መንስኤዎችን በመለየት መረጃ የመሰብሰብ የመተንተንና የመፍትሄ ሀሳብ የማቅረብ ስራ ይሰራሉ ተብሏል፡፡

በተጓዳኝም ከማዕከል እና ከክፍለ ከተማ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን መስሪያ ቤት ጋር በመቀናጀት የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎችን እንደሚሰሩ ተገልጿል፡፡

ወጣቶቹ ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የአምስት ቀን የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር የስልጠና መድረክ ተዘጋጀቶ በየካ ክፍለ ከተማ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.