Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የሚመራው የንግድ ስራ ቅልጥፍና ማሻሻያ ስራ ያለበትን ደረጃ የሚመለከት ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮሚቴው ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ የተጀመረው የንግድ ስራ ቅልጥፍና ማሻሻያ እንዲሳካ ተቋማት ግልፅ የመረጃ ልውውጥና መናብበ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገለጸ።

አገልግሎት ፈላጊዎች፣ ነጋዴዎችና አልሚዎች ባሉበት ቦታ ሆነው አልያም በአንድ መስኮት የተቀላጠፈ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ነው የተነገረው።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የስራ ምቹነትና ቅልጥፍናን ለመፍጠር ተቋማት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

የብሄራዊ ኮሚቴው አካል የሆነው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የንግድ ስራ ለመጀመር የሚያስችል መረጃዎችን የያዘ የንግድ መረጃ አቀባይ (business portal) business.gov.et አልምቶ ይፋ ማድረጉን ገልጿል።

መረጃ አቀባዩ ወደ ንግድ ስርዓቱ ውስጥ ለመግባት የሚፈልጉ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው የተሟላ መረጃ ለማግኘት የሚያስችላቸው ነው።

ንግድ ለመጀመርና ፍቃድ ለማውጣት የሚወስደው ጊዜ፣ የሚፈጀው ገንዘብ፣ መሟላት ያላባቸው መረጃዎች እና የመሳሰሉትንም የያዘ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አሀመዲን መሀመድ የንግድ ማኅበረሰቡና የመንግስት ሰራተኛ እውነተኛ የመረጃ መለዋወጫ እንዲኖረው እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፈው አመት በወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ በንግድ ስራ ቅልጥፍና ከዓለም ሀገራት 159ኛ ደረጃ ላይ ስትሆን በሚቀጥሉት አመታት ይህንን ደረጃ መቶዎቹ ዝርዝር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.