Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አዲስ የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የአስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሣ በክልሉ ከሚያስፈልጉ 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-
ዶክተር ካህሣይ ብርሃኑ …… የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ
ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ …… የኮንስትራክሽን፣ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ፋሲካ አምደ ስላሴ …… የጤና ቢሮ ሃላፊ
አቶ አበራ ንጉሴ ………. የፍትህ ቢሮ ሃላፊ
ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ ……… የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ
አቶ ዮሴፍ ተስፋይ ………. የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን …….. የትምህርት ቢሮ ሃላፊ
ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ ……. የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ሃላፊ
አቶ ሰለሞን አበራ …….. የውሃ ሃብት ቢሮ ሃላፊ
አቶ አብርሃ ደስታ ……. የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ እና
አቶ ገብረመስቀል ካሣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የጽህፈት ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸው ተገልጿል፡፡

ሌሎች ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣዮቹ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ ይገባሉ መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.