የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ህልፈተ ህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

By Meseret Awoke

December 24, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ህልፈተ ህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ነው ሃዘናቸውን የገለጹት፡፡

በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ህልፈተ ህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማቸውን ሀዘን የገለፁ ሲሆን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ መንግስት በአጥፊዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ህብረተሰቡም ተገቢውን እገዛ እንደሚያደርግ ፅኑ እምነት እንዳላቸው በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልፀዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!