Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው አዲስ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ መድረጉን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የመረጃ አሰባሰብ፣ አደረጃጀትና ስርጭትን ለማዘመን የሚያስችል አዲስ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው አዲስ ባበለጸገው የተቀናጀ የመረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓት አጠቃቀም ከአስር ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት በቢሾፍቱ ከተማ ለሁለት ቀን የሚቆይ የግንዛቤ ስልጠና እየሰጠ ነው ።

ትግበራው የመረጃ ስርዓት አስተዳደር፣ የመረጃ አሰባሰብና የስርጭት ስርዓቱን ማዘመን የሚያስችል መሆኑን ተናግሯል።

ስርአቱ ተጠቃሚዎች ባሉበት ሆነው የሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት የሚችሉበት መሆኑን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ የተጠቃሚዎቸ የመረጃ መረብ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

“ስርዓቱ ከማዕከል ጀምሮ እስከ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳና ቀበሌ ድረስ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ ታእማኒ፣ ተፈላጊና ዘርፈ ብዙ መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዝ ነው” ያሉት ደግሞ የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አሳልፈው አበራ ናቸው።

የህዝብና ቤት ቆጠራ፣ የግብርና፣ ጤና፣ የትምህርትና ሌሎች ነባር መረጃዎች ወደ ስርዓቱ መግባታቸውን አመልክተዋል።

ክሌሎችን ወደ ስርዓቱ እንዲገቡ እየተደረገ ነው ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ቤንሻንጉልና አፋር ክልሎች ወደ ተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ገብተው እየተጠቀሙ መሆኑን ገልፀዋል ።

ሱማሌና ሐረር ክልሎችም በቅርቡ ወደ ስርዓቱ እንደሚገቡም አመላክተዋል።

ጋምቤላ፣ ትግራይና ሲዳማ ክልሎችንም ወደ ሰርአቱ ለማሰገባት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በስርአቱ አጠቃቀም ላይ የሚኖር የአቅም ውስንነትን ከወዲሁ ለመቅረፍ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.