የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በወላይታ ሶዶ ከተማ የእሳት አደጋ የተከሰተበትን የገበያ ስፍራ ጎበኙ

By Tibebu Kebede

December 25, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በወላይታ ሶዶ ከተማ የእሳት አደጋ የተከሰተበትን የገበያ ስፍራ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሰሞኑ በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ የገበያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ከፍተኛ ንብረት መውደሙ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!