Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ስታካሂደው የነበረው ስምምነት ፍጻሜ አገኘ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ከተለየች በኋላ በሚኖራት የንግድ ግንኙነት ላይ ያተኮረው ስምምነት መቋጫ ማግኘቱ ተሰምቷል፡፡

የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከስምምነቱ በኋላ የራሳችን ህግ እና የራሳችንን ዕጣፈንታ በእጃችን አስገብተናል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ ወገኞች የተደረሰው ስምምነት ለአውሮፓ ጠቃሚ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ወራት የፈጀውን ስምምነት ተከትሎ ብሪታንያ በቀጣዩ ማክሰኞ ከአውሮፓ ህብረት የንግድ ህግ እንደምትወጣ ይጠበቃል፡፡

ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር በየዓመቱ የ660 ቢሊየን ፓውንድ የንግድ ስምምነት ማካሄዷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ይህም ህብረቱ ከካናዳ ጋር እንዳለው ዓይነት የንግድ ስምምነት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሊየን ሂደቱ አድካሚ እንደነበር ገልጸው ፍትሓዊና ሚዛናዊ የሆነ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.