ስፓርት

ጋና በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን አሰልጣኞችን አሰናበተች

By Tibebu Kebede

January 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋና እግር ኳስ ማህበር በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝ አባላት ማሰናበቱን አስታወቀ።

ማህበሩ የወንዶችና የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ እና ረዳቶቻቸውን ከስራ ማሰናበቱን አስታውቋል።

ስንበቱ በሁለቱም ጾታዎች የታዳጊ፣ ወጣትና ዋናውን ቡድን አሰልጣኞችና ረዳቶቻቸውን ያካተተ ነው።

ማህበሩ የአሁኑ ስንብት እያደረገ ያለው ማሻሻያ አካል መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ