Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮሌጅ አባልና የዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሩሲያ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ልዩ እና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮሌጅ አባልና የዲፕሎማቲክ አካዳሚ ዳይሬክተር አሌክሳንደር ቪ ያኮቬንኮን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና የዲፕሎማቲክ አካዳሚው የሚሰጣቸው ሥልጠናዎችና በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡

አምባሳደር አለማየሁ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ሰፊ ገለጻና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በበኩላቸው ስለ አካዳሚው ለሃገራቸው እና ለውጭ ዲፕሎማቶች ስለሚሰጣቸው  ሥልጠና አስረድተዋል፡፡

በሁለቱ ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ የሩሲያ እና አፍሪካ ግንኙነቶች የበለጠ ማጠናከር የሚቻልበት ሁኔታንም ተነጋግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ በስብሰባው ላይ አካዳሚው በ2021 ለ24 የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶችን በሁለት ዙር የአጭር ጊዜ ስልጠና ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም  አካዳሚው የሁለቱን ሃገራት ባህላዊ ልውውጥ እና የውጭ ግንኙነት  ፖሊሲ በማስተዋወቅ ረገድ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርበው ለመስራት እንደሚፈልግ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.