Fana: At a Speed of Life!

ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር ምቹ የሆነች ሃገርን መፍጠር ያስፈልጋል – አቶ ደመቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር እና ችግሩን ለመቅረፍ ምቹ የሆነች ሃገርን የመፍጠር ስራ መስራት እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የሰዎች ንግድ፣ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገወጥ መንገድ ሰውን ለስራ ወደ ውጭ ሃገር መላክ ወንጀልን መከላከል እና መቆጣጠር ብሄራዊ ምክር ቤት አመታዊ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በስብሰባው ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ፣ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

የውይይቱ አላማ በህገወጥ መንገድ ለስደት የሚዳረጉ ዜጎችን ለመቆጣጠር እና ለችግር እንዳይጋለጡ ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እና ያለፉትንም ለመገምገም ነው።

በዚህም በ2012 እና 2013 አመተ ምህረት በህገወጥ መንገድ ከሚሰደዱት በተሻለ የተመላሾች ቁጥር ከፍ ያለበት እንደነበር ተነስቷል።

በሌላ በኩል በቀጣይ ዜጎችን ከህገ ወጥ ስደት ለመታደግ ሃገርን ለመኖር ምቹ ማድረግ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩትን ስጋቶች ማስወገድ ያስፈልጋል ተብሏል።

ለዚህም መንግስት የሰላም የማረጋገጥ ስራ ላይ አተኩሮ እየሰራ እንደሚገኝ አቶ ደመቀ አንስተዋል።

በይስማው አደራው

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.