Fana: At a Speed of Life!

ሀገር ዓቀፍ የወባ ሳምንት ዘመቻ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2023ዓ.ም የወባ በሽታን ለማጥፋት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ ሀገር ዓቀፍ የወባ ሳምንት ዘመቻ በድሬዳዋ በይፋ ተጀምሯል፡፡
የዘመቻውን መጀመር ይፋ ያደረጉት የአስተዳደሩ ከንቲባ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ተወካይ አቶ መሃመድ አሚን በአስተዳደሩ ይሁን እንደ ሀገር ያለውን የወባ በሽታ ስርጭት ለማስወገድ የሚረዱ ተግባራትን በተለያዩ ጊዜያት በሚካሄዱ ሥራዎች በበሽታው የሚከሰተውን ህመምና ሞት በከፍተኛ ደረጃ መከላከል መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በዚህ ዘመቻ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በመጨመር፣ ለትንኝ መራቢያ ምቹ የሆኑ ቦታዎችን በማፅዳት፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፋሰስና በማዳረቅ፣ በኬሚካል የተነከሩ የአልጋ አጎበሮችን ዘወትር በመጠቀምና አጎበሮችን ለአላስፈላጊ አገልግሎቶች ከመጠቀም በመቆጠብ ነዋሪውን ጤናማ ለማድረግ ርብርብ ማድረግ አለብን ብለዋል፡፡
የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃለፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በበኩላቸው ÷ለፋብሪካዎችና ለትላልቅ ሆቴሎች ፍቃድ ሲሰጥም ሆነ ከተሰጠ በኋላ ለወባ ትንኝ መራቢያነት ምክንያት የሚሆኑ ፍሳሾችን በተመለከተ ክትትል መደረግ እንዳለበትም ነው የተናገሩት፡፡
እንዲሁም ወባን ለማጥፋት የተሰሩ ውጤታማ ሥራዎችን በተሻለ ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቅሰው ወባ ከሚከሰትባቸው ጊዜያት ቀደም ተብሎ የጥንቃቄ ስራዎችን በመስራት ወባን ለማጥፋት መረባረብ ተገቢ ነው ማለታቸውን ከድሬዳዋ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.