Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ኢንጂነር ታከለ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመሆን በክልሉ የሚገኙ ባህላዊ ወርቅ አምራቾችና ወርቅ ሽያጭ የሚካሄድበትን ስፍራ መጎብኘታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ጋምቤላ በወርቅ በተፈጥሮ ጋዝ ማዕድናት የታደለች ብትሆንም በአግባቡ መጠቀም አልተቻለም ነው ያሉት፡፡

እንዲሁም ህገወጥ አዘዋዋሪዎችና የመሰረተ ልማት ችግር ተግዳሮች መሆናቸውን ጠቅሰው አብዛኛው የወርቅ ምርትም በህገወጥ መንገድ ከሀገር እየወጣ ይገኛል ብለዋል።

ይህን አካሄድም ወደ ስርዓት እንደሚገባ ጠቅሰው ባህላዊ አምራቾችንም በተገቢው መንገድ በመደገፍ አቅማቸው እንዲያድግ እንደሚሰራም ነው የገለጹት።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.