Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ ከተማ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ዳር ማስዋብ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ   

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከባለሀብቶች ጋር በትብብር ከጥቁር ውሀ እስከ ሞኖፖል ድረስ የሚለማ 7 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ዳር ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ፕሮጀክቱ የከተማው አመራሮች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የሚዲያ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ በኢትዮጵያ ከተሞች ከሚለሙ ልማቶች በተለየ መልክ የሚሰራው ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ሀዋሳ ከተማን ከምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ ከተማ ያደርጋታል ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማን ውብ፣ ጽዱ፣ አረንጓዴና ለኑሮ ምቹ የማድረግ ሁሉም ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ የለማች ከተማ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ በጋራ መስራት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

የፕሮጀክቱ አማካሪ አቶ አማረ አሰፋ በምስል የተደገፈ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፕሮጀክቱ ለከተማዋ የአረንጓዴ ውበት ከመስጠት ባለፈ ልዩ ልዩ መዝናኛ ስፍራዎችን እንዳካተተ መግለፃቸውን ከከተማው ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ፕሮጀክቱን የሚያለሙ የተቋማት ተወካዮች በበኩላቸው የሀዋሳ ከተማ የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ለማልማትም ምቹ መሆኗን ገልጸው ከተማዋን ከኢትዮጵያ ከተሞች ቀዳሚ ለማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፦

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.