የሀገር ውስጥ ዜና

በ500 ሺህ ብር የተገነባው የቡና ኮንትራት አስተዳደር ሶፍትዌር ስራ ጀመረ

By Feven Bishaw

December 25, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን 500 ሺህ ብር ወጪ ያደረገበት የቡና የኮንትራት አስተዳደር ሶፍትዌር ስራውን ጀመረ፡፡

የግብር ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን የኮንትራት ውል አስተዳደር ወደ ስራ መግባቱ የተንዛዛውን የግብይት ስርዓት ከማስቀረት ባሻገር ረጅም ጊዜ የሚፈጀውን የግብይት ሂደት በ5 ደቂቃ እንዲያልቅ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ህገ ወጥ ግብይትን እና ኮንትሮባንድን ያስቀራል ተብሏል፡፡

በባለስልጣኑ ግቢ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ የቡና ጥራት መመርመሪያ፣ የቅምሻ እና የባሬስታ ማሰልጠኛ ማዕከል ስራ ጀምሯል፡፡

ይህም ኢትዮጵያ ዘንድሮ ለምታዘጋጀው የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ውድድር የራሱን አስተዋፅኦ ያበረክታል ነው የተባለው፡፡

የግንባታው ሙሉ ወጪም በተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት (ዩኒዶ) እና በጣሊያን ኮርፖሬሽን ተሸፍኗል፡፡

በሲሳይ ሃይሌ