Fana: At a Speed of Life!

የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ ሌላ ያለአግባብ ሀብት የማፍራት ወንጀል ምርመራ ተጀመረባቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ተስፋ ኪሮስ ከዚህ በፊት ከተጠረጠሩበት ሌላ ያለአግባብ ሀብት የማፍራት ወንጀል ምርመራ ተጀመረባቸው፡፡
ተጠርጣሪው የህወሓት የፀረሰላም ቡድንን በገንዘብ በመደገፍ ወንጀል ከአንድ ወር በላይ ምርመራ ሲካሄድባቸው መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በትናትናው ዕለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የ100 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ የፈቀደ ቢሆንም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የሙስና ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ተጠርጣሪው ላይ አዲስ መዝገብ ከፍቶባቸዋል፡፡
መዝገቡ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የተከፈተ ሲሆን ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ተጠርጣሪው በችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ይታያል፡፡
ተጠርጣሪውን ያለአግባብ ከፍተኛ ሀብት በማፍራት ወንጀል ጠርጥሮ ምርመራ የጀመረባቸው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ከእሳቸው ጋር በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ የተፈቀደላቸው 2 ተጠርጣሪዎች በዚያው በተጠረጠሩበት መዝገብ ፖሊስ ይግባኝ ብሎባቸዋል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.