Fana: At a Speed of Life!

ግምቱ 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ዘጠና ሶስት ኩንታል ባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለበት ቅቤ ወደ ገበያ ሊቀርብ ሲል ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 17 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግምታዊ ዋጋው 1ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ዘጠና ሶስት ኩንታል ባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለበት ቅቤ ወደ ገበያ ሊቀርብ ሲል መያዙን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
ቅቤው የተያዘው በደቡብ ክልል ከፋ ዞን ዋቻ ከተማ አስተዳደር ቁሉሽ ቀበሌ ከተለያዩ ባለድርሻ አካለት ጋር በመተባበበር በታህሳስ 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም. በገበያ ላይ በተደረገ ኦፕሬሽን መሆኑን የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ በቃሉ አረጋ ÷ በኦፕሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከከፋ ዞን ጤና መምሪያ፣ ከደቡብ ከልል ልዪ ሀይል ፣ ከከፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ፣ ከዋቻ ወረዳ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በከፍተኛ የዞኑ አመራሮች በመታገዝ በተሳካ ሁኔታ ምርቱን መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።
አያይዘውም ፖሊስ ቀጣይ ምርመራዎችን ለማድረግ ኤግዝቢት መደረጉንም ገልጸዋል ፡፡
በዓላት በሚደርሱበት ወቅት በህብረተሰቡ በስፋት በሚፈለጉ ምርቶች ላይ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀል አላግባብ የሆነ ትርፍ ለማጋበስ የሚሮጡ የህብረተሰቡንም ጤና ለጉዳት የሚዳርጉ ግለሰቦች እየተስተዋሉ መሆኑንም ተመላክቷል።
በመሆኑም እነዚህን ህገወጦች ለማስቆም ማንኛውም የህገወጥ የምግብና መድኃኒት ንግድ ፣ዝውውር እንዲሁም ምግብን ከባድ ነገር ጋር የሚደባልቁ በጋራ ለመከላከል ህብረተሰቡ አቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ ፣ለፍትህ አካለት አሊያም በነጻ ስልክ መስመር በ8482 በመጠቆም የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ጥሪ አቅርቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.