Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ የመከላከያ ሰራዊት የህግ ማስከበር ተልዕኮን ለማገዝ አስተዋጽዎ ላበረከቱ የአፋር ክልል የፀጥታ ሀይሎችና ለአካባቢው ነዋሪዎች የምግብ ቁሳቁስ አበረከተ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀገር መከላከያ ሰራዊት የህግ ማስከበር ተልዕኮውን ለማገዝ አስተዋጽዎ ላበረከቱ የአፋር ክልል የፀጥታ ሀይሎችና በአካባቢው ለሚገኙ ነዋሪዎች የምግብ ቁሳቁስ አበረከተ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህወሓት ጁንታ ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በከፈተው ጥቃት ሳቢያ በተለያዩ አጎራባች ክልሎች በህግ ማስከበር ስራ ለተሳተፉ የልዩ ሀይል እና የሚሊሻ አባላት እንዲሁም የተፈናቀሉ ዜጐችን ለመደገፍ ቃል በገባው መሠረት ነው 2ሺህ 400 ኩንታል እህል ለአፋር ክልል ያስረከበው ።
ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ እና የአዲስ አበባ ከተማ አቃቢ ህግ ቢሮ ኃላፊ አብዱልቃድር መሀመድ ለአፋር ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ሀላፊ ለአቶ መሀመድ ሁሴን አስረክበዋል ።
በዚህ ወቅት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕከት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላደረገው ድጋፍ በክልሉ ሕዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጁንታው የጥፋት እኩይ ተግባር ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን ለመደገፍ ለአፋር ክልል 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት እና 94 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ በጠቅላላው 100 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.