የሀገር ውስጥ ዜና

ዶክተር ሊያ ታደሰ በፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆስፒታል የማድረግ እንቅስቃሴን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

December 28, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በባህር ዳር በሚገኘው ፈለገ ሕይወት ሆስፒታል የንፁህና ደህንነቱ የተጠበቀ ሆስፒታል የማድረግ እንቅስቃሴን ጎበኙ፡፡

ሚኒስትሯ በተጨማሪም በኤሌክትሮኒክስ የታገዘ የጤና መዛግብት አፈፃፀም እና የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች ህሙማንን ማዕከል ያደረጉ እንዲሆኑ ለማስቻል የተሰራውን ስራም ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝታቸው ወቅትም በቁርጠኝነት የሚሰሩ የሆስፒታሉንና የክልሉ ጤና ቢሮ አመራሮችንና ሰራተኞችን አመስግነዋል፡፡