ቢዝነስ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

By Tibebu Kebede

January 03, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ኢንስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሀገሪቱን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል ከታህሳስ 25 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ አሁን በስራ ላይ ባለው የመሸጫ ዋጋ ሆኖ እንዲቀጥል መወሰኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በታህሳስ ወር ሲሸጥ ከነበረበት በሊትር 28 ነጥብ 24 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 1 ብር ከ08 ሳንቲም ቀንሶ በሊትር ብር 27 ነጥብ 16 እንዲሸጥ ተወስኗል።

በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑም ሚኒስቴሩ አስታውቋል።