Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን 16 ሺህ አባ ወራዎች ከፀሐይ ብርሃን ሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የሚኖ ከተማ 16 ሺህ አባ ወራዎች ከፀሐይ ብርሃን ሚመነጭ ኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ።

ከዞኑ ዋና ከተማ ሐረር ከ250 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ በምትገኘው የሚኖ ከተማ አገልግሎት የጀመረው የፀሐይ ኃይል ፕሮጄክቱ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በፌዴራልና በክልሉ መንግስት ትብብር የተሰራ ነው ተብሏል።

ከዋናው ኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመር በርቀት የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን የኤሌከትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘው ዕቅድ አንዱ አካል የሆነው የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፀሐይ ብርሃን ሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታ ከተጠናቀቀ ሰባት ወራትን አስቆጥሯል።

የከተማዋ አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ የፕሮጄክቱ ሁለተኛው ዙር ማስፋፊያ ሲጠናቀቅ ለ26 ሺህ አባ ወራዎች አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

ቁምቢ ወረዳ የመስኖና ኢነርጂ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መሀማድ ሳኒ በአሁኑ ወቅት ከ850 በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቆጣሪዎችን በሚኖ ከተማ ለመትከል እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁንም 150 ቆጣሪዎች ተከላ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ መንግስት ከአየር ብክለት የጸዳ ኢኮኖሚን እውን ለማድረግ እየሰራቸው ካሉ ትልልቅ ፕሮጄክቶች መካከል ይህኛው በሀገሪቱ ካሉት መሰል ፕሮጄክቶች ውስጥ ሁለተኛው ነው ማለታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

 

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.