Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ የ10 ዓመት መሪ ዕቅድላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመጭው የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በውይይት መድረኩ ላይ ከተማ አስተዳደሩ የሀገሪቱን የብልፅግና ትልም ዕውን ለማድረግ ካወጣው ዕቅድ የተቀዳ የ10 አመት መነሻ ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።
መዳረሻ ዕቅዱ የተሟላና የከተማዋን ነዋሪዎች ፍላጎት ያካተተ እንዲሆንም በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር በማድረግ ጠቃሚ ግብአት ማሰባሰብ አስፈላጊ መሆኑንም አቶ ጃንጥራር ጠቅሰዋል።
የ10 አመቱ ዕቅድ የህዝብን አንገብጋቢ ጥያቄዎች ለመመለስ ያለመ በመሆኑ ከህዝብ የሚገኘውን ጠቃሚ ግብአት በማካተት ዕቅዱን የመከለስ ስራው በቅርብ ቀን ይጠናቀቃል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኘላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር መስከረም ምትኩ በበኩላቸው÷ በተዘጋጀው የ10 አመት ዕቅድ ዙሪያ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከርና ለእቅዱ ግብአት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.