Fana: At a Speed of Life!

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፕላንና ልማት ኮሚሽን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተወያየ።

የኢኮኖሚ የልማት ዕቅድ፣ የመሰረተ ልማት ዕቅድ፣ የማህበራዊ ዘርፍ ልማት ዕቅድ፣ የፍትህ ዘርፍና የሕዝብ አገልግሎት ዕቅድ፣ የሰላም ግንባታ እና ቀጠናዊ የጋራ ልማት ዕቅድ በ10 ዓመቱ የልማት ያላቸው ቦታ ተነስቷል።

ግብርና በተመለከተ የመስኖ አቅምን በማጎልበት የግብርናን ዘርፍ ከዝናብ ጥገኝነት ማላቀቅ፣ የዘመናዊ የእርሻ አገልግሎትን ማስፋፋት፣ በከፍተኛ ምርታማነታቸው የሚታወቁ አነስተኛ አርሶ አደር የተሻለ የመሬት ይዞታ እንዲኖራቸው ማገዝ እና ቀስ በቀስ ወደ ባለሃብትነት ለማሳደግ መታቀዱ ነው የተገለፀው ።

ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ አደረጃጀትና አሰራር፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ/ኦቶሜሽን፣ የክትትልና ግምገማ ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግም ተጠቅሷል፡፡

ከማምረቻ ዘርፍ ጋር በተያያዘ የነባር ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ ግብዓቶችን ለሚጠቀሙ ቅድሚያ መስጠት፣ በተለይ በምግብ፣ በጨርቃጨርቅና በመድሀኒት ላይ በማተኮር መስራት ፣ የኢንዱስትሪውን የእሴት ሰንሰለት፣ ትስስርና ተመጋጋቢነትን ማጠናከር፣ አዳዲስ ኢንቨስትመን በብዛት በጥራት እና በአይነት ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ መርህን የተከተለ ልማት ትኩረት መስጠት፣ ከባድ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ የኬሚካልና የፋርማሲቲካልስ ኢንዱስትሪዎች ልማትንና ከሌሎች ኢንዱስትሪዎች ጋር ያላቸውን ትስስር ማጠናከርም ትኩረት የተደረገበት ጉዳይ ነው ተብሏል።

የማዕድን ዘርፍ በተመለከተም የውጪ ምንዛሬ ግኝትና የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ ፣ በዘርፉ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት  እና ዕሴት የሚጨምሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በዘርፉ ኢንዲስፋፉ ማድረግ ሌላኛው እቅድ መሆኑም ተነስቷል፡፡

የከተማ ልማት ዘርፍን አስመልክቶም በሥራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት ሂደት አምራች ዘርፎች ላይ ማትኮር፣ የካፒታልና የሰው ኃይል ፍልሰትን በየአካባቢው በመግታት የገጠር፣ ኢንደስትሪያላይዜሽንን ማስፋፋትና ለመካከለኛ ከተሞች እድገት ልዩ ትኩረት መስጠት፣ ልማትን ለማፋጠንና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የመሬትአቅርቦት ሥርዓት መዘርጋት፣ የመልሶ ማልማትና የማስፋፊያ ሥራዎችን ነባር ተጠቃሚዎችን አካታች ባደረገ ሁኔታ ተፈጻሚ ማድረግ፣ የከተማ መሬት ምዝገባና ካዳስተር ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገኝበት ተነግሯል።

የቱሪዝም ዘርፍ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ፣ ኢነርጂ ፣ ውሃ፣ መስኖ ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፣ የትምህርት ዘርፍ ፣ የጤና ዘርፍ፣ የሴቶች፣ የሕጻናትና የወጣቶች ልማት፣ የፍትህ ዘርፍ፣ የሰላም ግንባታ ልማት፣ የውጭ ጉዳይና ቀጠናዊ የጋራ ልማት ዙሪያን በተመለከተ ለምክር ቤቱ አባላት ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በይስማው አደራው

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.