Fana: At a Speed of Life!

የሕወሓት የጥፋት ቡድን ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሕወሓት የጥፋት ቡድን ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው ተገኙ።
የሕወሓት የጥፋት ቡድን በተደጋጋሚ ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና አስመራ ሲያስወነጭፋቸው የነበሩት ተተኳሽ ሮኬቶች በመቐለ ከተማ በግለሰብ መጋዘን ውስጥ ተከማችተው መገኘታቸውን የልዩ ዘመቻ ኮማንድ አስታውቋል።
የመከላከያ ሠራዊት መቐለ ከተማን ከተቆጣጠረ በኋላ የልዩ ዘመቻ ኮማንድ 2ኛ ብርጌድ አንድ ወጋገን ሻለቃ ባደረገው አሰሳ እና ፍተሻ በመጋዘን ውስጥ ያልተተኮሱ 13 ሮኬቶች የተገኙ ሲሆን፣ 7 ሮኬቶች ደግሞ ከማስቀመጫው ሳጥን ወጥተው ተተኩሰው እንደነበርም አስታውቋል።
በተጨማሪም የተተኳሽ ሮኬት ማስወንጨፊያ ከባድ ተሽከርካሪ ከመቐለ ከተማ ዳርቻ ባለ ስፍራ ተደብቆ መገኘቱን ኢቢሲ ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.