Fana: At a Speed of Life!

በማዕድን ዘርፉ ሀገራዊ ፍላጎት ላይ ማተኮርና የውጪውን ገበያ ማሳደግ ቀጣይ የተኩረት አቅጣጫዎች ናቸው – ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕድን ዘርፉ ሀገራዊ ፍላጎት ላይ ማተኮርና የውጪውን ገበያ ማሳደግ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ እምቅ ሀብት የተለዩ ቦታዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን በተመለከተ ለረጅም ጊዜ የተጠኑ ጥናቶችን በጋራ በማደራጀት ለምርት ዝግጁ የሆኑ ቦታዎች መለየታቸውንም አንስተዋል፡፡
የተዘጋጁት ቦታዎች ስራቸውን በተገቢው መንገድ ባለማከናወናቸው ፍቃዳቸው ከተሰረዙ ተቋማት የተነጠቁ ቦታዎች የተካተቱበት መሆኑን የገለፁጹት ኢንጂነር ታከለ በቀጣይ ጊዚያት ቦታዎቹ ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ተቋማት ክፍት እንደሚሆኑ ተናግረዋል።
ቦታዎቹን ወደስራ ለማስገባትም በቅርብ ጊዜ ዓለም አቀፍ ጨረታ ይወጣልም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ያሏትን የማዕድንና ነዳጅ ሀብቶች በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን በመሳብ መገናኛ ብዙሀን ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.