Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ጥቃት እንዲደርስ ሚስጥራዊ መረጃ ለህወሓት አመራሮች ሲያቀበል ነበር የተባለ የአየር መንገዱ የአይ ሲቲ ባለሙያ ፍርድ ቤት ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ጥቃት እንዲደርስ የአየር መንገዱን ሚስጥራዊ መረጃ ለህወሓት አመራሮች ሲያቀበል ነበር የተባለው የአየር መንገዱ የአይ ሲቲ ባለሙያ ፍርድ ቤት ቀረበ።
ግለሰቡ ይርጋ ገብረመድህን እንደሚባልም ነው የተገለጸው።
መርማሪ ፖሊስ ለምርመራ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ስራ ለችሎቱ አቅርቧል።
በዚህም ተጠርጣሪው በአየር መንገዱ በሚሰራበት አይ ሲቲ ሙያ በስራ አጋጣሚው የሚያገኛቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለቡድኑ ሲልክ እንደነበር ባገኘሁት ማስረጃ አረጋግጫለው ሲል ለችሎቱ አብራርቷል።
በተጨማሪም ተጠርጣሪው በክልሉ ህገወጥ ምርጫ እንዲካሄድ ሲያመቻችና በምርጫውም ተሳታፊ እንደነበር በማስረጃ አረጋግጫለው ብሏል።
ከዚህም ባለፈ ግለሰቡ በራሱ ድረገጽ የተለያዩ መረጃዎችን ውጭ ላሉ ተባባሪዎች ሲልክ እንደነበር መረጃዎች አሉኝ ሲል ገልጿል።
በመሆኑም ለጀመርኩት ምርመራ ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ሲል ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ፖሊስ ጠይቋል።
ተጠርጣሪውም ከጠበቃ ጋር ችሎት የቀረበ ሲሆን ÷ ጠበቃውም ደንበኛዬ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የለውም ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜ ሊፈቀድ አይገባም ሲሉ ተከራክረዋል።
በዋስ ተለቆ ጉዳዩን በውጭ ይከታተል ሲሉ የዋስትና ጥያቄ አንስተዋል።
መዝገቡን የመረመረው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ ያስፈልገዋል ሲል 10 ቀን ፈቅዷል።
ውጤቱን ለመጠባበቅ ለታህሳስ 30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.