Fana: At a Speed of Life!

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ጋር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት ደህንነቱ የተጠበቀ ዳታ ሴንተር ለመገንባት በሚያደርገው ሂደት የማማከር ስራን ለማከናወን የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የመግባቢያ ስምምነቱን የፈረሙት የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ወርቁ÷ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት እራሱን በማዘመን ረገድ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ኤጀንሲው የተሰጠወን የማማከር ሃላፊነት በቁርጠኝነት እንደሚወጣ ተናግረዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም የፋይናንስ ተቋማት ካለባቸው የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት አንፃር ኤጀንሲው ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሆነ ጠቁመው÷ የኢትዮጵያ መድህን ድርጅት የመንግስት ልማት ተቋም ከመሆኑ አንፃር የሚኖርበትን የሳይበር ደህንነት ተጋላጭነት ለመቅረፍ በማማከር ዘርፈ ከፍተኛ ሃለፊነት ወስዶ ይሰራል ብለዋል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መንግስቱ መሃሩ በበኩላቸው÷ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት በዘርፉ በቂ ልምድ ያለው በመሆኑ በዳታ ሴንተር ግንባታው ውስጥ የሚኖረው ፋይዳ ዘርፈ ብዙ መሆኑን አንስተዋል።
በተለይ ተቋሙ የሚገነባው ዳታ ሴንተር ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የእውቀት ሽግግር እንዲኖር እንዲሰራም ጥሪ አቅርበዋል።
የማማከር ስራው አንድ አመት ከስድስት ወር የሚወስድ ሲሆን የዳታ ሴንተሩ ከሚገነባበት ጊዜ አንስቶ የደህንነት ፍተሻ እስከማደርግ የሚዘልቅ እንደሆነም ተነግሯል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በኢንሹራንስ ዘርፍ በ2025 በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰራ እንደሆነ ሲገለፅ ስምምነቱ ይህንን በማሳካት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው መገለጹን ከኢመደኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.