Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ስር ነቀል ለውጥ ላይ ትገኛለች – አምባሳደር ግርማ ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ኢትዮጵያ ስርነቀል ለውጥ እያደረገች መሆኑን ከአናዶሉ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታወቁ፡፡

አምባሳደር ግርማ ተመስገን በቆይታቸው በወቅታዊው የኢትዮጵያ ሁኔታ እና በትግራይ ክልል ስለተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ በተመለከተም ገልጸዋል፡፡

በገለጻቸውም የህወሓት ቡድን ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስታውሰዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም መንግስት ተገዶ ወደ ህግ ማስከበር ዘመቻ ገብቷልም ነው ያሉት አምባሳደሩ፡፡

በአሁኑ ወቅትም መንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻውን ማጠናቀቁን ገልጸው መሰረተ ልማቶችን መልሶ ወደ ስራ ማስገባት፣ በህግ ማስከበር ዘመቻ ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ማጠናከር የመንግስት ትኩረት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በሌላ በኩል የጥፋት ኃይሉ ባሰማራቸው ግለሰቦችና በሚከፍላቸው መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ሐሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተካሄዶብኛል በማለት የተዛቡ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝም ነው የገለጹት፡፡

በተጨማሪም የጥፋት ኃይሉ ንጹኃንን ዒላማ ያደረገ ጭፍጨፋ በማይካድራ መፈጸሙን ጠቅሰው ይህ የቡድኑ ባህሪ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ነገሩን በቅርብ ለሚያውቀው በአካባቢው የሚገኘውን መሰረተ ልማት ለሚታዘብ እና የትግራይ ክልል ህዝብን የኑሮ ደረጃ ለሚመለከት ሰው የጥፋት ኃይሉ ራሱን እንጂ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ እንዳላደረገ ይገነዘባልም ብለዋል፡፡

አምባሳደር ግርማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ በሃገሪቱ በርካታ ለውጦች መታየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታን የሚያሳድግ ስር ነቀል ለውጥ እየተካሄደ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያና ቱርክ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት አወድሰው አንካራ የኢትዮጵያ ወዳጅ መሆኗን ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም የሃገራቱን 125ኛ አመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.