ህወሓት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን በመቐለ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ከህወሓት መሰረታዊ ድርጅቶች የተወከሉ አባላት፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ድርጅቱ እያካሄደ በሚገኘው አስቸኳይ ጉባኤ የኢህአዴግን ውህደት በሚመለከት ተወያይቶ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።