የሀገር ውስጥ ዜና

‘ራይዚንግ ኢትዮጵያ’ በሚል ሃሽታግ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጀመረ

By Abrham Fekede

December 30, 2020

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ራይዚንግ ኢትዮጵያ በሚል ሃሽታግ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ዛሬ ተጀምሯል፡፡

ዘመቻው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ቱሪዝም ኢትዮጵያ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያን በትብብር የተዘጋጀ ነው።

ባለፉት ወራት የተሳሳቱ የመገናኛ ብዙኃን ትርክቶችን ለማረቅና የኢትዮጵያን መልካም ጎን ለማስተዋወቅ ያለመ ዘመቻው ነው ተብሏል፡፡

ዘመቻው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችን እንደሚያስተባብር ተገልጿል፡፡

በዘመቻው ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት እምቅ አቅም፣ ባህል፣ የመስህብ ስፍራዎችን፣ በጎ አድራጎትን እና ፕሮጀክቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያስተዋውቃል ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!