Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚሰሩ 554 ወጣቶችን ወደ ሥራ አስገባ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ በአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚሰሩ 554 ወጣቶችን ወደ ሥራ ማስገባቱ ተገለፀ።

ወጣቶቹን ወደ ሥራ ለማስገባት የአምስት ቀን ስልጠና ሰጥቶ መጨረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ወጣቶቹ በተለይ ኢንዱስትሪዎች እና ሌሎች አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የሚያስከትሉትን የአካባቢ ብክለት ለመከላከል የመፍትሔ ሐሳቦችን የማቅረብ ብሎም ተቋማቱን የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባር ያከናውናሉ ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሲሳይ ጌታቸው፥ በመዲናዋ የሚታየውን የአካባቢ ብክለት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ወጣቶችን አሰልጥኖ ማሰማራት ማስፈለጉን ተናግረዋል።

ወጣቶቹም የተለያዩ ተቋማት የሚያስከትሉትን የድምፅ፣ የፍሳሽ እና የደረቅ ቆሻሻ ብክለት መንስኤዎችን በመለየት የመፍትሔ ሐሳብ ያቀርባሉ ብለዋል።

ተቋማቱን የመከታተልና የመቆጣጠር ተግባርን ጨምረው እንደሚያከናውኑም አብራርተዋል።

ለመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ከተማ አስተዳደሩ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በመመደብ ሥልጠና እንደሰጠም አውስተዋል፡፡

የወጣቶቹ የሥራ ተሞክሮ እየታየ ሌሎች ወጣቶችንም አሰልጥኖ ወደ ሥራ የማስገባት እቅድ መያዙን ጠቁመዋል፡፡

ሥልጠናውን የወሰዱ ወጣቶች ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ውል በመፈጸም በየወረዳቸው በኢንተርፕራይዝ በመደራጀት የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ያከናውናሉ።

በመሠረት ውባየ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.