Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሂሩት በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የኢራን አምባሳደር ሳማድ አሊ ላኪዛዴህ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ።

ሚኒስትሯ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየውን ታሪካዊ ግንኙነት አስታውሰው ይህንን ታሪካዊ ወዳጅነት አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በተለይ በባህል፣ በቱሪዝምና በስፖርት መስክ የተደረጉትን የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶች እንደገና ማደስ እንደሚያስፈልግ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

በቅርቡም ረቂቅ የጋራ መግባቢያ ሰነድ አዘጋጅተው እንደሚልኩ እና እንደሚፈረም የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.