Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ እያስመዘገበ ላለው አመርቂ የስራ አፈጻጸም ገንዘብ ሚኒስቴር ምስጋና አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለወሰዳቸው እርምጃዎች ምስጋና አቀረበ፡፡

ዛሬ የአየር መንገዱ የስራ አፈጻጸም በገንዘብ ሚኒስቴር በተገመገመገበት ወቅት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የአየር መንገዱ አመራር በወሰዳቸው ፈጣንና ፈጠራ የተሞላበት እርምጃዎች አሁን ለተገኘው ውጤት ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በአየር መንገዱ የተወሰዱ የአመራር ውሳኔዎች አየር መንገዱን ከአፍሪካ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ እንዲሆን እንዳስቻለውም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት፥ አየር መንገዱ በዚህ ወቅት ውጤታማ መሆን የቻለው የቦርዱ አመራር፣ አስተዳደር አካላትና ሰራተኞች ቁርጠኛና ጠንካራ የስራ ባህል ስላላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሌሎች አየር መንገዶች ኪሳራ ሲደርስባቸውና ሰራተኞቻቸውን ሲበትኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በማስፋፋትና ትኩረቱን በመለዋወጥ በተለይም የካርጎ፣ የጥገና እና የሆቴል አገልግሎቶችን በስፋት በማከናወን የተሻለ ገቢ ማግኘት እንደቻለ መናገራቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ተወልደ አያይዘውም አውሮፕላን ማረፊያዎች እና ተርሚናሎች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በቀጣይነት እንደሚገነቡ ገልፀዋል፡፡

አየር መንገዱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን በመከላከል የመንገደኞቹንና የሰራተኞቹን ጤንነት ለመጠበቅ የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ የሰው ህይወት በማዳን ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ መሆኑም በግምገማው ወቅት ተብራርቷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.