የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆነ

By Tibebu Kebede

December 30, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆኗል፡፡

የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻው ከታህሣሥ 21 ቀን 2013 እስከ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት፣ የተለያዩ ውሎችና የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ዳያስፖራና ኤምባሲዎችን በማንቀሳቀስ በማህበራዊ ድረ ገፅ የሚካሄድ ነው ተብሏል።

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ዘመቻው የቱሪዝም ሀብትን ይበልጥ በማስተዋወቅ ተደራሽነታቸውን በማስፋት የጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

የሃገሪቱን ገፅታ የበለጠ ለመገንባትና ከኮቪድ 19 በኋላ በርካታ የውጭ ጎብኚዎችን ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለውም ነው የተባለው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!