የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

By Tibebu Kebede

December 30, 2020

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በጋምቤላ ክልል የጤና ስራዎች ላይ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር መከረ።

በውይይቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፥ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦሞድ ኦጁሉ እና የክልሉ የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል።

ከክልሉ ኮቪድ 19 ግብረ ሃይል ጋር የኮሮና ቫይረስን በመከላከል እና በመቆጣጠር ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፥ ያጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ የመከላከል ስራውን ለማጠናከር የታሰበውን ንቅናቄ አስመልክቶ ውይይት መደረጉን ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።

እንዲሁም በክልሉ የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር እና የጊኒ ዎርምን ከማጥፋት አንጻር በሚታዩ ክፍተቶች ላይም ውይይት ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!