Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ እዝ ለ3 ወራት ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 300 በላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ እዝ በማዕረግ እድገትና በአቅም ግንባታ ስልጠና ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን ከ1 ሺህ 300 በላይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት አስመርቋል።

ለሦስት ወራት ሥልጠናቸውን ተከታትለው የተመረቁት የታችኛው የአመራር አባላት ሲሆኑ፥ ከመካከላቸውም የማዕረግ እድገት የሚሰጣቸው ሠልጣኞች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ዛሬ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ በሚገኘው የዕዙ ማሰልጠኛ ማዕከል በተካሄደው የምረቃ ሥነ ሰርዓት ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ ተገኝተዋል።

ሥልጠናው በፀረ ሽብር በተለይም በቀጠናው ካለው የአልሸባብ እና ሌሎች የሽብር ቡድኖች እንቅስቃሴን ለመግታት በሚቻልበት አግባብ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የአሁኑ ሥልጠና የሠራዊቱን አቅም ከፍ ለማድረግና የሚሰጠውን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም እንዲችል መሆኑ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ያለምንም እንከን በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቅ የሚያስችል ዝግጅት ላይ ያተኮረ ስልጠናም ማግኝታቸው ታውቋል።

ሠልጠኞቹ ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሥልጠና የተሰጣቸው መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም የተሰጠው ሥልጠና የሠራዊቱን አቅም ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳም ተጠቁሟል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.