Fana: At a Speed of Life!

በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት ተግባር ላይ ምክክር ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግብርና ሚኒስቴር በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ስርጭት ተግባር ላይ ከክልሎች ጋር የሚሰራውን የቅንጅት ስራ ላይ የጋራ ምክክር አደረገ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት በአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ስርጭት ተግባር የ2012/13 ምርት ዘመን አፈጻጸምና እና የ2013/14 ምርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት ምን መሆን እንዳለበት ከኦሮሚያ ክልል ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት ምርት ግብይት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ ግብርና ለኢትዮጵያ ክፍለ ኢኮኖሚ ዋናው መሰረት መሆኑን ጠቅሰው  ዘርፉን በግብዓትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ግብርናን የማሻገር ስራ መሰራት እንዳለበት በተለይ በማዳበሪያና ምርጥ ዘር ላይ የአርሶ አደሩን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል አቅርቦት ማከናወን የሚጠበቀውን ምርትና ምርታማነት ለማምጣት ዋናው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ግብዓት አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ተስፋ ከምንጊዜም በላይ በ2012/13 የምርት ዘመን ውጤታማ የሆነ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት እንደነበረ ገልጸዋል፡፡

ከ18 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሞ በመጓጓዝ ላይ እንዳለና የተከናወነበት የግዥ ሂደት እና ወደ ሀገር ቤት እየገባ ያለበት ጊዜ ከምንጊዜም በላይ ፈጣን መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር አቶ ኡመር ሁሴን ፈታኝ ነገሮች ቢኖሩም ከበፊቱ የተሻለ ስራ ለመስራት  ያለውን አቅም አሟጠን መጠቀም አለብን ብለዋል፡፡

በቀጣይ በሌሎች ክልሎችም ተመሳሳይ የውይይት መድረኮች እንደሚኖሩ በውይይቱ ላይ መገለጹን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.