Fana: At a Speed of Life!

በዲላ ሠላም ሆስፒታል ከአንዲት እናት 26 ኪሎ ግራም ዕጢ ወጣ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በዲላ ከተማ በሚገኘው ሠላም ሆስፒታል አንዲት እናት 26 ኪሎ ግራም የሚመዝን ዕጢ በቀዶ ህክምና እንደወጣላቸው የሆስፒታሉ ሐኪም አስታወቁ።

ቀዶ ህክምና ያደረጉት የሆስፒታሉ ሐኪም ዶክተር ጌታቸው መርጊያ የ40 ዓመት ዕድሜ ያላቸው እኚህ እናት ሆዴ አብጧል ብለው ወደ ጤና ተቋሙ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ምርመራ ሲካሄድም ከማህጸን ተነስቶ ሁሉንም የሆዳቸው አካባቢ የሸፈነ ዕጢ መኖሩ በመረጋገጡ ቀዶ ህክምና እንደተደረገላቸው አስረድተዋል።

በቀዶ ህክምና የወጣለቸው የዕጢው ክብደት 26 ኪሎግራም የሚመዝን መሆኑን ዶክታር ጌታቸው አመልክተው ችግሩን ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ቀዶ ህክምናው ሰላሳ ደቂቃ መፍጀቱን የተናገሩት ሐኪሙ ከቀዶ ህክምናው በኋላ እናቲቱ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

ላለፉት አራት ዓመታት ሆዳቸው እየገፋ በመሄዱ በሚኖሩበት ምዕራብ ጉጂ ዞን ሃንባላ ዋማና ወራዳ ጎሮ ባደሳ ቀበሌ የተለያዩ ባህላዊና ዘመናዊ ምርመራ ሲያደርጉ ቢቆዩም መሻሻል አለመታየቱን የታካሚዋ የመጀመሪያ ልጅ ተናግሯል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የእናታቸው ሆድ በማበጥ እየደከማቸውና መንቀሳቀስ እያቃታቸው መምጣቱን ተከትሎ የተሻለ ህክምና ፍለጋ ወደ ዲላ መምጣታቸውንም ነው የተናገረው።

ዲላ በሚገኘው ሠላም ሆስፒታል በተደረገላቸው የቀዶ ህክምና ዕጢ ሆኖ ተገኝቶ በመውጣቱ መደሰቱን ገልጾ÷ ሂደቱ በዚህ መልኩ በሠላም ይጠናቀቃል የሚል ግምት እንዳልነበረውም አስረድቷል።

ከቀዶ ህክምናው በኋላ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የተናገረው ልጃቸው እናታቸው እሱን ጨምሮ ሶስት ልጆች እንዳላቸው መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.