Fana: At a Speed of Life!

በህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ድንበር ሲያቋርጡ የነበሩ 11 ዜጎች ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ድንበር በማቋረጥ ላይ የነበሩ 11 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሱን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያውያኑ በህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎች አማካኝነት በተሰጣቸው የተሳሳተ መረጃ ከሚኖሩበት አካባቢ በመነሳት ያለበቂ የጉዞ ሰነድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ድንበር በማቋረጥ ኬንያ ከገቡ በኋላ በኬንያ የወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በዚህም ከወንጀል ምርመራ ቢሮው ጋር በቅንጅት በመስራት ዛሬ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤምባሲው ባለፉት ስድስት ወራት 263 ዜጎችን ከኬንያ ኢሚግሬሽን፣ ከኬንያ ወንጀል ምርመራ ዳይሬክቶሬት እና ከኬንያ የፖሊስ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ታስረው የነበሩ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለሱ ይታወሳል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.