Fana: At a Speed of Life!

በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ቦርድ ረቂቅ መመሪያዎች ላይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የቦርዱ ሰበሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የፓርቲዎቹን መገኘት አመስግነው፤ ፓርቲዎቹ በረቂቅ መመሪያዎቹ ላይ ያላቸውን ገንቢ አስተያየቶች እንዲያካፍሉ ጥሪ አድርገዋል።

ረቂቅ መመሪያዎቹ ቦርዱ በኢትዮጵያ የምርጫ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 47 ንዑስ አንቀጽ 3 እና አንቀጽ 57 ንዑስ አንቀጽ 4 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ነው መድረኩን ያካሄደው፡፡

በዚህም የድምፅ አሰጣጥን፣ ቆጠራንና የምርጫ ውጤት አገላለጽ ሂደት አፈጻጸምን ግልጽና ቀልጣፋ ለማድረግ፤ እንዲሁም የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣ የዕጩ ወኪሎች፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች፣ የሀገር ውስጥና የዓለም ዐቀፍ ታዛቢዎች በእነዚህ ሂደቶች ላይ ወጥነት ያለው አሠራር እና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ተብሎ የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህን በማስመልከት የመድረኩ አቅራቢ የሆኑት ዶክተር ጌታቸው አሰፋ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የገቢ፣ የወጪና የንብረት አስተዳደር እና ሪፖርት አቀራረብ መመሪያና የድጋሚ ምርጫ አፈጻጸምን የተመለከቱት ረቂቅ መመሪያዎችን ጨምሮ የመድረኩ አቅራቢ በሆኑት ባለሙያዎች በዶክተር ጌታቸው፣ ሰለሞን ግርማና ዳኛቸው መለሰ ማብራሪያ መሰጠቱ ተገልጿል፡፡

ማብራሪያዎቹን ተከትሎ በሁለት ዙር ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጋር የቦርዱ አመራር በሆኑት አቶ ውብሸት አየለ መድረክ መሪነት የፓርቲ ተወካዮቹ ሀሳብና አስተያየት እንዲሰጡበት መደረጉም ተጠቅሷል፡፡

ፓርቲዎቹም እንዲብራራላቸው የፈለጉትን አንቀጽና ቢጨመር ያሉትን ሀሳብ አጋርተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ባለሙያዎቹ የፓርቲ ተወካዮቹ ባቀረቧቸው አስተያየቶች መሠረት ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

ፓርቲዎቹ የሚኖራቸውን አስተያየቶች በመድረኩ ሳይወሰኑ በጽሑፍም ማቅረብ እንደሚችሉ ባለሙያዎቹ ገልጸዋል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.