Fana: At a Speed of Life!

በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቸውን እና መደምሰሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ የጁንታው ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች መማረካቸውን እና መደምሰሳቸው ተገለጸ፡፡

ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮቹ በተካሄደ ዘመቻ መማረካቸውን እና መደምሰሳቸውን የመከላከያ ሐይል ሥምሪት መምሪያ ሐላፊ ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው አረጋግጠዋል፡፡

በውጭ የሚገኙ የጁንታው ሚዲያዎች የሐሰት ኘሮፓጋንዳ ቢያናፍሱም የመከላከያ ሐይልና ፌደራል ፖሊስ በቅንጅት በወሰዱት እርምጃ በርካቶች ተማርከዋል ነው ያሉት።

ከዚህ ባለፈም እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑት መደምሰሳቸውንም ተናግረዋል፡፡

የቀሩትም በየእምነት ተቋማትና ገዳማት፣ ዋሻና ሸለቆዎች እራሳቸውን ደብቀው እንደሚገኙ መረጃ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ጁንታው የሞቱበትን ከፍተኛ አመራሮቹን ከሰብአዊ ርህራሄ ውጭ በሆነ መልኩ እንዳይታወቁ ለየብቻ ስለሚቀብራቸው ለመለየት አዳጋች መሆኑንም አብራርተዋል።

የጁንታ ሐይል ተደምስሷል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ በየሸለቆው የደበቃቸው የህዝብና የመንግስት ንብረት መያዙንም አስረድተዋል፡፡

ጁንታው በህይወት እንዳለ በአንዳንድ አካላት ከውጭ የሚነዛው ኘሮፖጋንዳ ፍፁም ሐሳት እንደሆነ መናገራቸውንም ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.