Fana: At a Speed of Life!

በመንደር መሰባሰብና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ከሱማሌ ክልል ጋር በመተባበር በክልሉ በመንደር ማሰባሰብ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ያላቸው የማህበራዊና ኢኮኖማዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ በጅግጅጋ ከተማ ወርክሾፕ አዘጋጅቷል።

ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የፌዴራሊዝምና የልዩ ድጋፍ ጀነራል ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ደገፋ ቶሎሳ የወርክሾፑ አላማ ህብረተሰቡ በመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም ያገኛቸውን መልካም ነገሮች፣ ያጋጠማቸውን ፈተናዎች እና ያሉበትን ሂደት አይቶ እና ገምግሞ የተሻለ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ብለዋል።

የሱማሌ ክልል የርዕሰ መስተዳደር  ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ የሱፍ በበኩላቸው ባለፋት ሁለት የለውጥ ዓመታት በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ማስፈን በመቻላችን  ትኩረታችንን ልማት ላይ አውለናል ብለዋል።

በሱማሌ ክልል የመንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም ያሉ ዕድሎችና  ያጋጠሙ ፈተናዎች በሚል ርዕስ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቧል።

ረዳት ፕሮፌሰር መሀመድ አብደላ እና ረዳት ፕሮፌሰር ነጂብ አብዲ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ አርብቶ አደሮች በመንደር ከተሰባሰቡ በኃላ የተሻለ የትምህርት፣ የጤና እና የሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ ቢሆኑም አሁንም በርካታ ጉድለቶች እንዳሉባቸዉ ገልፀዋል ።

ከ60 በመቶ በላይ በመንደር የተሰባሰቡ ዜጎች በፕሮግራሙ ደስተኛ መሆናቸውን የገለጸው ጥናቱ አሁንም የሚጠቀሙት የእርሻ መሳሪያ ኋላ ቀር መሆን፣ ደረጃቸዉን የጠበቁ ጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት አለመኖር እና የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ማነስ አሁንም የአርብቶ አደሩ ችግሮች መሆናቸው ተመልክቷል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.