Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 388 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 810 የላቦራቶሪ ምርመራ 388 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 124 ሺህ 652 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 155 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ 251ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ 14 ህይወት አልፏል።

ይህንን ተከትሎም ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 937 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 10 ሺህ 462 ሰዎች መካከል 245 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 806 ሺህ 46 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.