Fana: At a Speed of Life!

397 ተጨማሪ ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 532 የላቦራቶሪ ምርመራ 397 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትናንትናው ዕለት 74 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ 325 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 944 ደርሷል።

እስካሁን በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 811 ሺህ 578 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

በሀገሪቱ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 125 ሺህ 49 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 10 ሺህ 778 ሰዎች መካከል 235 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.