የሀገር ውስጥ ዜና

በሰመራ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው 13ኛው የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ እየተፋጠነ መሆኑ ተገለጸ

By Tibebu Kebede

January 02, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ የፊዚካል አፈፃፀሙ 70 በመቶ መድረሱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ።

የፓርኩ ግንባታ ከ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ በቻይናው ሲ ሲ ሲ ሲ ተቋራጭ ስራው እየተከናወነ ይገኛል።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ በመንግስት እየለሙ ከሚገኙ ፓርኮች 13ኛው ነው።

የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአሁኑ ወቅት እለታዊ የግንባታ እድገቱን አንድ በመቶ በማድረስ በአጭር ግዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።

በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ የሚገኘው ይህ ፓርክ ጠቅላላ ስፋቱ 2 ሺህ . ሄክታር ላይ ያረፈ ነው።

ፓርኩ ሲጠናቀቅ የሎጅስቲክ ፓርክ በመሆን ሌሎቹን ፓርኮች ያስተሳስራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሌሎች ምርቶችም ተመራጭ የሚያደርጉት ብዙ አማራጮች የያዘ ፓርክ መሆኑን ኮርፖሬሽን ገልጿል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!