Fana: At a Speed of Life!

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ471 ሚልየን ብር በላይ በቦንድ ግዥና በስጦታ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 25 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ471 ሚልየን ብር በላይ በቦንድ ግዥና በስጦታ ተሰበሰበ ።
471 ሚሊየን ብሩየህዳው ዋንጫ በክፍለ ከተማው በቆየባቸው የ25 ቀናት ቆይታ ውስጥ በቦንድ ግዥና በስጦታ የተሰበሰበ ሲሆን÷ ዋንጫውንም ለቦሌ ክፍለ ከተማ አስረክቧል::
በዋንጫ ርክክብ መርሃ ግብሩ ላይም ከአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለስ አለም ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮችና ነዋሪዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ፣ ዋንጫውን የተረከበው የቦሌ ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል ።
አቶ መለሰ ዓለሙ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ÷በራስ አቅም ይህን የታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በኢትዮጵያዊነት ወኔ በመስራት ከድህነት ለመውጣት የሚታትሩ ህዝቦች መሆናችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ ትልቅ ተምሳሌት የሆነ የዚህ ትውልድ አሻራ የሆነ ፕሮጀክት ሲሆን÷ፕሮጀክቱ ታሪክ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን መነሳትንም ጭምር የሚያሳይ እና ሲጠናቀቅ ከድህነት በመላቀቅ ወደ ብልፅግና መሸጋገር የምንችልበት አብሳሪ ፕሮጀክት ነውም ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ መለሰ አያይዘውም ወቅቱ ከኮቪድ ጋር ተያይዞ እና አፍራሽ ሀይሎች በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና ያለበት ወቅት ሲሆን በዚህ ደረጃ በቦንድ ግዢ እና በስጦታ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ ለኢትዮጵያ ብልፅግና ቆርጦ የተነሳ ህዝብ ያለ መሆኑን ለወዳጅም ለጠላትም የሚያሳይ አኩሪይ ተግባር ተከናውኗልም ነው ያሉት።
በዚህ የድጋፍ ተግባር ላይ የተሳተፉና ያስተባበሩ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አጠቃላይ አመራሮች ፣ ባለሀብቶች ፣ የተለያዩ ተቋማት እንዲሁም የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አቶ መለሰ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ ለግድቡ በቦንድ ግዥና በስጦታ አስተዋፆ ላበረከቱ ለሁሉም ወረዳዎች እና ተቋማት የዋንጫና የምስጋና ምስክር ወረቀት እንደተበረከተላቸው ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.