Fana: At a Speed of Life!

የግል የጤና ተቋማት እንዲጠናከሩ መንግስት የበኩሉን ጥረት ያደርጋል- ዶ/ር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ) የግል የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ የሚሰጡት የጤና አገልግሎት ከፍተኛ በመሆኑ ለዘርፉ መጎልበት መንግስት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ።
ሚኒስትሯ ይህንን የገለጹት መቀመጫውን በሀዋሳ ያደረገው አላቲዮን ጠቅላላ ሆስፒታል አዲስ ያስመጣው ባለ 64 እስላይስ ሲ.ቲ ስካን ወደ ስራ ባስገባበት ወቅት በክብር እንግድነት ተገኝተው ነው።
በወቅቱም የስቲ ስካኑ ወደ ስራ መግባት ለበርካታ ዜጎች አግልግሎቱን በቅርበት ለመስጠት እንደሚያስችልም ተመላክቷል።
ዶክተር ሊያ የግል ጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ የጤና አገልግሎት ከመስጠት አንፃር የጎላ ማና ያላቸው በመሆኑ መንግስት በጋራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ መንግስት በቀጣይ አስር አመታት ለመተግበር ባዘጋጀው የጤና እቅድ ላይ ከግሉ ዘርፍ ጋር በጥልቀት ለመስራት የሚያስችል መርሃግብር መካተቱንም ጠቁመዋል።
አያይዘውም ለጤና አገልግሎት የሚሆኑት መሳሪያዎችን ከውጭ ማስገባት ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እንደሚጠይቅ ያነሱት ሚንስትሯ ከፋይናንስ ተቋማትም ጋር በጋራ እንደሚሰራም ነው የተናገሩት ።
ከዚያም ባለፈ የሀዋሳ ከተማን የሜዲካል ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የግል ባለሀብቶች እንዲሳተፉም ሀሳብ አቅርበዋል ።
የሲዳማ ክልላዊ መንግስት ምክትል የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ሌታሞ በበኩላቸው÷ በአሁን ላይ በክልሉ 219 የግል የጤና ተቋማት ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል።
ሃላፊው አያይዘውም ዘርፉ እንዲጠናከር የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ ያደርጋልም ነው ያሉት።
ዶክተር ይድነቃቸው ገብረመስቀል የአላትዮን ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤትና ሜዲካል ዳይሬክተር በበኩላቸው ÷ባለ 64 ስላይስ ሲ.ቲ ስካን መሳሪያ በኢትዮጵያ በጥቂት የጤና ተቋማት ብቻ እንደሚገኝ ጠቅሰው ማሽኑ ወደ ሀዋሳ መምጣቱ ለደቡባዊ የሀገሪቱ አከባቢ የህብረተሰብ ክፍልን አገልግሎት በመስጠት የህብረተሰቡን እንግልትና ወጪ ይቀንሳል ብለዋል።
መሳሪያው በሌሎች ማሽኖች የማይታዩ እጅግ ጥቃቅን የውስጥ ደዌዎችን በጥራት የማስመልከት አቅም እንዳለውም ዶክተር ይድነቃቸው ማብራራታቸውን ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በሲዳማ ክልል የሚገኙ የጤና ተቋማትን በመጎብኘት ላይ መሆናቸው ይታወሳል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.